የቅዱሳን ሕይወት

 

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ

የቅዱስ ሙሴ የወንድማማችነት ህብረት

በከፊል ከሚከተለው ድረገጽ የተወሰደ፡  http://grforafrica.blogspot.com/2015/08/moses-ethiopian-black-saint-teacher.html

 


የቅዱስ ሙሴ የወንድማማችነት ህብረት

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ በመጀመሪያ የወንበዴዎች መሪ፣ ገዳይ እና በጥንታዊቷ አፍሪካም ሌባ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እሱ የለውጥ አርአያ ሆነ፡፡ ከአፍሪካ ቅዱሳኖች መካከል የሱ የሚያስደምም ነው፡፡ ከባርነት ያመለጠው ሙሴ የ 75 ሌቦች አለቃ ነበር፡፡ ከዱርዬዎቹ ጋር ሙሉ ከተማዋን ያሸበረ ግዙፍና ሃይለኛ ሰው ነበር፡፡ ሙሴ የተለወጠው እሱና ቡድኑ ለስርቆት ቤተ ከመቅደስን ያጠቁ ጊዜ ነበር፡፡ እዛ አንድ ስነ-ስርኣት ያለው ሰው አገኘውና በጣም ተነካ፡፡ በቅጽበትም ስለሰራቸው ሀጥያቶች ጸጸት ተሰማው፣ ንስሃም ገባ እናም እዛው ቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዲቆይ ለመናቸው፡፡ ሙሴ ለአመታት በድሮ ህይወቱ ተሰቃየ፤ እናም ወደነበረው መንገዱም ለመመለስ ጓጓ፡፡ አንድ ቀን ሀጥያቶቹን ለ ቅዱስ ማካሪየስ በመናዘዝ ላይ ሳለ አንድ መልአክ የሀጥያቶቹን ዝርዝር ይዞ በፊቱ ቀረበ፡፡ ሲናዘዝም መልአኩ ሀጥያቶቹን አንድ በአንድ መሰረዝ ጀመረ፡፡ ብዙ ሲናዝዝ ብዙ ይሰርዝለታል፡፡ ቅዱስ ማካሪየስንና ቅዱስ ኢሲዶርን ክተዋወቀ በኋላ የቀድሞ መንገዱን እርግፍ አድርጎ ትቶ መነኩሴ ሆነ፡፡ ከዛም ቅዱስ ሙሴ ለቅስና ተሸመ፤  ይህ ለበረሃ አባቶች አንድ አንዴ የሚገኝ ክብር ነው፤ ሄዶም 75 መነኩሳን ያሉበት ቤተ መቅደስ አገኘ፣ ልክ እንደ ቀድሞው ሌቦቹ ቁጥር፡፡ በጥበቡ፣ በትህትናው፣ በፍቅሩ እናም ማንም ላይ ባለምፍረዱ ይታወቅ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ወንድም በተመሳሳይ ሃጥያት ከተያዘ በኋላ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዩ ቅዱስ ሙሴ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጥቶ ፍርድ እንዲፈርድ ጠየቀው፡፡ እሱም ሳይፈልግ በጀርባው አሸዋ የተሞላበት ቀዳዳ ቦርሳ ይዞ ሄደ፡፡ ከቦታው ሲደርስ የተያዘው ወንድም ለምን እንደዚህ አይነት ነገር እንደተሸከመ ጠየቀው፡፡ እርሱም ቀለል አድርጎ “ይሄ አሸዋ የሌላ ሰው ሀጥያት ለመፍረድ ስሄድ ከኋላዬ እየቀረ የመጣው ሃጥያቶቼ ነውˮ አለው፡፡ ይህንን መልስ ሰምተው ሀጥያተኞቹ  ወንድሞች የበደላቸውን ይቅር በማለት የሌሎች ወንድሞች ሀጥያት ላይ ከማተኮር ይልቅ የራሳቸው ድነት ላይ ማተኮር ጀመሩ፡፡

በ405 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ቤተ መቅደሱ በዱርዬዎች ተጠቅቶ በ 75 አመቱ ቅዱስ ሙሴ  አረፈ፡፡ በነሀሴ 22ም ተዘክሮ ይውላል፡፡ የወንድማማችነታችንም ጠባቂ ነበር፡፡

    

                                          የቅዱስ ሙሴ ቅሬታ ወደተገኘበት የስኬቲስ ሸለቆ ቅዱስ ባራሙስ ገዳም

 

ስለ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ ቪድዮ :

 

                                                             ዝግጅት በ: ሃ. ጎ. ፣ ሮ. ኢ.