መሠረታዊ ኦርቶዶክስ አስተምህሮ

 

ውነት ማነው?

ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት

ምንጭ: https://www.vimaorthodoxias.gr/theologikos-logos-diafora/spoudi-stin-eikona-tis-metamorfoseos-tou-sotiros/

 

 

ጌታችን ለጴንጤናዊው ጲላጦስ እንዲህ አለውእኔ ስለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደዓለም መጥቻለሁ ጲላጦስም በጥርጣሬእውነት ምንድን ነው?› ብሎ መለሰለት፡፡ ጥያቄው መልስ እንደሌለው በማመንም ከክርስቶስም ሆነ ከሌላ መልስ አልጠበቀም፡፡ ነገር ግን ወደ አይሁዳውያን ሄደ።

ጲላጦስ ትክክል ነበር። በአእምሮችን ፍጹሙ እውነትን የዓለማት ህልውና ሁሉ ስር አድርገን ካሰብነው  "እውነት ምንድን ነው?" ለሚለው ጥያቄ መልስ አይኖርም።

ነገር ግን ጲላጦስ ጥያቄውን መጠየቅ በነበረበት አግባብ፡- "እውነት ማነው?" ብሎ ጠይቆ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ ከዚያን ጊዜ በፊት በመጨረሻው እራት (ጸሎተ-ሐሙስ) ዕለት ጲላጦስ እንደሚጠይቀው አስቀድሞ ተገንዝቦ (ዐውቆ) ለተወደዱ ደቀመዛሙርቱና በእነርሱ በኩል ለመላው ዓለም 'እውነት እኔ ነኝ' ብሎ የመለሰውን መልስ ያገኝ ነበር።

ሳይንስና ፍልስፍና በራሳቸው ጥያቄውን እውነት ምንድን ነው? በሚለው አገላልፅ አስቀምጠዋል፤ የክርስትና ሃይማኖት አስተሳሰብ በአንጻሩ እውነትን ሁልጊዜ 'ማነው?' በሚለው ይመለከተዋል።

ሳይንቲስቶችና ፈላስፎች ጥቂት በማይባል አጋጣሚ ክርስቲያኖችን ይህን በማለታቸው ሚዛናዊ ያልሆኑ ቅዥታሞች አድርገው ይመለከቷቸዋል፤ በአንጻሩ እነርሱ ራሳቸውን በጽኑ መሠረት ላይ በማቆም እርግጠኞች (አዎንታዊያን) ነን ይላሉ። እውነትን "ምንድን ነው?" የማለትን አሉታዊነት በትክክል አይገነዘቡትም። እነርሱ ትክክለኛውና ፍፁም የሆነው አገላለፅ እውነትምንድን ነው?› እንጂ 'ማነው?' ብቻ ሊሆን እንደሚችል (እንደሆነ) አይረዱም፡፡ እውነት ረቂቅ የሆነ ቀመር ወይም ዐሳብ አይደለም ራሱ ሕይወት እንጂ።

እውነት "ምንድን ነው?" ከማለት በላይ በእርግጥ አሉታዊ የሆነ ነገር ምን ሊሆን ይችላል? ይህን መሰል አስገራሚ ተፃራሪነት ከአዳም መውደቅ ጀምሮ በሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ እናስተውላለን። ሰው አመክንዮአዊ በሆነው አእምሮው በመሳብ ተመርዞ ስለሚኖርእውነት ምንድነው?› የሚለው ጥያቄ የሚነሣው ከሳይንስ እና ፍልስፍና (ለምሳሌ እንደ ጲላጦስ) ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ በሆነው የሰው ሕይወት ውስጥም ሰዎች ያለማቋረጥ አውነትንምንድን ነው?› በሚል ታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ሊያገኙት ሲጥሩ እናገኛቸዋለን፡፡ 

'ምንድን ነው?' ብለው ፈልገው ከእውነታ ላይ ከደረሱ፣ ልዩ ኃይል የሚኖራቸውና ውስንነት የማይኖርባቸው የህያዋን ሁሉ ጌታ እንደሚሆኑ ያስባሉ። ሰው በሃይማኖት ሕይወቱ ውስጥ አመክንዮአዊ ምርምርን ካስገባ እርሱ ያለጥርጥር ለዓለም የሚኖረው አቋም ሁሉ አምላክ ነው እንደሚሉት አሕዛባውያን (ፓንቴይስቶች) ነው። አምላኩን የሚፈልግ አዕምሮ ሁልጊዜ በራሱ አቅም ስለ እግዚአብሔር እውነታ ለማወቅ በሞከረ ቁጥር፣ ቢረዳውም ባይረዳውም ሳይንስና ፍልስፍና እንዲሁም ፓንቴይስቶች እውነትን 'ምንድን ነው?' ብለው ወደ ገቡበት ተመሳሳይ ስሕተት ውስጥ ይወድቃል።

እውነት 'ማነው?' ማለት ምክንያት በማስቀመጥ በፍፁም አይደረስበትም። እግዚአብሔር 'ማነው?' የሚለው የሚታወቀው ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በማድረግ ብቻ ሲሆን ያም በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብቻ ነው። ገዳማዊው አረጋዊ አባ ሲሎአንም ለዚህ ተደጋጋሚ አጽንኦት ይስጣሉ፡፡

ጌታችን እራሱ ስለዚህ ሲናገርየሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል : አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን : በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን_ _ _ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል ብሏል።

ኦርቶዶክሳዊው የትሕርምት ልምምድ ረቂቅ የሆነ ማሰላሰልን አይቀበልም፡፡ ስለ እግዚአብሔር ማሰብን በረቀቀ መንገድ ስለ መልካም፣ ውበት፣ ዘለዓለማዊነት፣ ፍቅርና ወዘተረፈ በማሰላሰል ላይ የሚገድብ ማንኛውም ሰው የተሳሳተ መንገድ ላይ ያለ ነው፡፡ ራሱን ከተግባራዊ ነገሮች እና ዕሳቤዎች ብቻ ፈጽሞ የሚያርቅም እውነተኛውን መንገድ አላገኘውም፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ስለ እግዚአብሔር ማሰላሰል ስለ መልካም፣ ፍቅርና የመሳሰሉ ነገሮችን በተመለከተ የሚደረግ ረቂቅ የሆነ ማሰላሰል አይደለም፡፡ አእምሮን ተግባራዊ ከሆኑ ነገሮችና ዕሳቤዎች ሁሉ ማራቅም አይደለም፡፡ እውነተኛ ማሰላሰል ወደ ነፍስ በመምጣቱ በኩል በእግዚአብሔር የሚሰጥ ነው፡፡ ከዛም ነፍስ ስለ እግዚአብሔር ማሰላሰል ትጀምራለች፡፡ በዚህም እርሱ ወዳጅ፣ መልካም፣ አስደናቂ፣ ዘለዓለማዊ መሆኑን እና ሰማያዊ እና ከመረዳት በላይ መሆኑን ትመለከታለች፡፡ ነገር ግን በረቀቀው መንገድ ምንም ነገር ማሰላሰል አይቻልም።

ተጨባጭና እርግጠኛ በሆነው እውነተኛ መንሳዊ ሕይወት ውስጥ ምናባዊነት ምንም ቦታ የለውም። ከእግዚአብሔር ጋር አማናዊ የሆነ ኅብረት የሚገኘው አካላዊ ወደ ሆነው አምላክ ጸሎት በማድረግ ነው፡፡ እውነተኛ የሆነ ክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ልምምድ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ ነው፤ ይሄም በሰው ፈቃድና ጥረት ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም፤ ይሄንንማ ክርስቲያን ያልሆኑትም ሊለማመዱት ይችላሉና፡፡

ዝግጅት : . .


ምንጭ: http://www.oodegr.com/