የቅዱሳን ሕይወት

 

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዜግነትን መሠረት አድርጋ ቅዱሳንን አትለይም። የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን የግሪክ ፣ የሩስያ ፣ የሮሜንያ፣ የሞልዶቫ፣ የኢትዮጵያ ፣ የግብፅ፣ የሶርያ እና አልፎ ተርፎም ከምዕራብ (ከካቶሊክ) ቤተከርስቲያን ጋር ከመለያየቷ በፊት የነበሩ የእንግሊዝ ደሴቶች እና ሌሎች የአውሮጳ እና የስካነዲኔቪያ ግዛቶች ቅዱሳንን በሙሉ ትቀበላለች። ቅዱሳን ማለት በኑሮአቸው እና በመሥዋዕትነት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር የገለጹ ሲሆኑ እንደ እግዚአብሔር ሕግ የኖሩ ሰማዕታት ፣ ጻድቃን አበው እና እማትንም ይጨምራሉ። የቅድስና ልምምድ ከፍትወታትና ከኃጢአት ራስን ማንጻት ፣ አብርሆት እና በሂደት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ ሲሆን በምንኩስናም ሆነ በትዳር ሕይወት ያሉ በሙሉ በዘመናት ሁሉ ወደዚህ ጉዞ (ሕይወት) ተጠርተዋል።

‡  ቅዱስ ፉልቪያን-ማቴዎስ (St. Fulvian-Matthew) ኢትዮጵያ ንጉስ

‡  ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ

‡  ቅዱስት ማክሪና የቅዱስ ባሲሊኦስ ታላቅ እህት