OODE ምንድነዉ

 

OODE የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖትን አስተምህሮዎች ለማጥናት፣ በማስረጃ በማደራጀት ተደራሽ ለማድረግና ለኅትመት (ለንባብ) ለማብቃት የተዘጋጀ የኤሌክትሮኒክ መድረክ ነው። መድረኩ በተለያየ የዕድሜ ክልልና የሥራ መስክ ላይ በሚገኙ ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መስፋፋት (ለወንጌል መሰበክ) ቅድሚያ በሚሰጡና ጊዜያቸውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ለማጥናትና ለዓለም ለማድረስ በሚያውሉ ግለሰቦች የሚዘጋጅ ነው እንጂ በቀጥታ ከየትኛውም አጥቢያ ጋር ግንኙነት የለውም። OODE ምንም ዓይነት የገንዘብ ድጎማም አያገኝም፤ የኢንተርኔት ወጪና አንዳንድ ክፍያዎች የሚሸፈኑት በአባላቱ ነው። የጥናት ውጤታቸውን የሚያጋሩና በትርጉም ሥራ የሚሳተፉ አባላቱ በሙሉ ሁሉም በሚጋሩት የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለመጠበቅ ባላቸው ተናሣሽነት በነጻ ፈቃድ የሚሳተፉ ናቸው።

OODE የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን በየጊዜው እያዘጋጀ ለንባብ የሚያበቃ መድረክ ነው። ይህ የኢንተርኔት ድረ-ገጽ በአሁኑ ጊዜ በሰባት ቋንቋዎች ማለትም በግሪክኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣልያንኛ፣ሮሜንያኛ፣ቱርኪኛ ና ፋርሲ የተዘጋጁ ድረ-ገጾችን ይይዛል። የአማርኛ ድረ-ገጹ እንዲኖረው የተደረገበት ምክንያትም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትውፊት ካለን ቅርበትና ዕውቀት የተነሣ ነው።

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ከቅድመ-ኬልቄዶን ጀምሮ የነበረውን ጥንታዊ ሃይማኖትና ትውፊት ክርስትና በአዋጅ የአክሱማዊው ሥርወ መንግሥት ሃይማኖት ከሆነበት ጊዜ አንሥቶ በጥቂቱ ለ፲፻፮፻ ዓመታት ጠብቀው አቆይተዋል። የሮማ መንግስት  ግዛት ከመስፋቱና ለኢትዮጵያም ቅርብ ስለነበረ እንደ ድልድይ ሆኖ ከግርክና ስርያ ክርስትና አገናቸዉ። ቤተክርስቲያኗ ከቅብ ቤተክርስቲያን ጋር የእኅትማማች ግንኙነት ያላት ሲሆን የመጀመርያው የኢትዮጵያ ፖትርያርክ አቡነ ባስልዮስ በ ፲፱፻፶፩ መሾማቸውን ተከትሎ እስኪቋረጥ ድረስም ጳጳሳት እየተሾሙ የሚመጡት ከግብጽ ነበር። የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አንድምታ  የተከተሉት የተርጉም ትዉፈት የ ሶስት መቶና የሌሎች የቤተ ክርስትያን አባቶች መሆኑ ይታወቃል።

ምንም እንኳ እምነቱ የተነሳው ከሀዋርያት አስተምህሮ ነው ቢሉም ይህ ልማድ በኩሽና ሴም በባህልና በፖሊቲካዊ ምክንያቶች ቄሳውስትና የእምነት አስተማሪዎች የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እንዴት በትክክል እንደሚያስተምሩ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በእነዚህ አመታት ውስጥ ለአስተምህሮቹ ከነበረው አቀባበል የተነሳ ተጠብቆ ቆይቷል፡፡

ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያዳከሟት ታሪካዊ ክስተቶች እንዳሉ ሆነው የአብነት ትምህርት ቤቶች መዳከም እና መዛባት ምእመኑን በተወሰነም ቢሆን ከአባቶች አስተምህሮ እንዲርቅ ያደረገው ይመስላል። OODE በነገረ መለኮት ኮሌጆች፣ በነገረ መለኮት ምሩቃን እና በማኅበረ ቅዱሳን ምእመኑን ወደ አባቶች አስተምህሮ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ያደንቃል። የአማርኛ ድረ-ገጹ ዋና ራእይም የእነዚህ አካላትን ጥረት ማገዝና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በጥናት የታገዙ ጥልቅ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን በአማርኛ ማድረስ ነው። ዋና ዓላማውም አማኞች ዋና ዋና በሚባሉ ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ልምምዶች ማለትም በንስሓ ሕይወትና በሱታፌ አምላክ(እግዚአብሔርን በመምሰል ማደግ) እንዲጠነክሩ ማገዝ ነው።

ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዓለምን ሙሉ ያቀረ ነዉ። ሌላው የዚህ ገጽ ዓላማ የግርክና የኢቲዖጵያ ኦርቶዶክሳውያን ቤተክርስቲያናትን አራርቀው ያቆዩትን ታሪካዊና ሌሎች ችግሮች ለመፍታት ይረዳ ዘንድ ኦርቶዶክሳዊ አቀባበልና (የችግር አፈታት) መግባባት ማስፋት ነው።

ምንም ስንኳ አንዳንዶቻችን አማርኛ ማንበብና መጻፍ ብንችልም አብዛኞቹ ትርጉሞች ላይ አማርኛ ተናጋሪ በሆኑ ሰዎች ድጋፍ አጊኝተናል። ከOODE ዓላማ ላለማፈንገጥ ስንልም የጸሐፊዎችን ስሞች ሳናካትት የስሞችን የመጀመርያ ፊደላት ብቻ እንደምንጠቀም እናሳውቃለን።በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያውያን የነገረ መለኮት ተማሪዎችንና ምሩቃንን በትርጉም እንዲያግዙን ለመጋበዝ እንፈልጋለን። በትርጒም ሥራው ላይ ሲሳተፉ የአባቶችን ትምህርቶች ለማንበብና ለመረዳት የበለጠ ዕድል የሚከፍት መሆኑ የታመነ ነውና።